ማጠቃለያ
Read the full fact sheet- ከአስጨናቂ ወይም አስፈሪ ክስተት በኋላ ጠንካራ ምላሽ መኖሩ ለእርስዎ የተለመደ ነው። አሳዛኝ ክስተት ሲባል የሚከተለው ሊሆን ይችላል፥ የጫካ እሳት ወይም ጎርፍ በእርስዎ ላይ የተፈጸመ ወንጀል ወይም የጥቃት ድርጊት የመኪና አደጋ አካላዊም ሆነ ፆታዊ ጥቃት ሲፈፀምቦ ስለ አስጨናቂ ክስተቶች ፎቶዎችን፣ የዜና ዘገባዎችን ወይም የማህበራዊ ሚዲያ ልጥፎችን ማየት።
- የተለያዩ አካላዊ፣ አእምሯዊ፣ ስሜታዊ እና የባህርይ ምላሾች ሊያጋጥምዎት ይችላል። ግን ለመቋቋም እና ለማገገም ብዙ ማድረግ የምትችላዋቸው ነገሮች አሉ።
- ከ 3-4 ሳምንታት በኋላ አሁንም የስሜት ቀውስ ምልክቶች ከታዩ እርዳታ ማግኘት አስፈላጊ ነው።
On this page
እርዳታ የት እንደሚገኝ
- የእርስዎ ኣጠቃላይ ሓኪም (ዶክተር)
- እንደ የአእምሮ ሐኪም፣የስነ ልቦና ባለሙያ፣ አማካሪ ወይም ማህበራዊ ሰራተኛ ያሉ የአእምሮ ጤና ባለሙያዎ
- የአካባቢዎ የማህበረሰብ ጤና ጣቢያ
- የአውስትራሊያ የስነ-ልቦና ማህበረሰብ ሪፈራል አገልግሎት ቴለ. 1800 333 497
- ፎኒክስ አውስትራሊያ የድህረ-የስሜት ቀውስ አእምሯዊ ጤና ማዕከልቴለ. (03) 9035 5599
- የሀዘን እና የዘመድ ሞት ሀዘን ማዕከል ቴለ. 1800 642 066
ነፃ የስሜት ቀውስ ስፔሻሊስት እርዳታ፥
- የወንጀል ሰለባ ከሆኑ፡ victimofcrime.vic.gov.au/services-for-victims-of-crime-[amharic] ይጎብኙ። እንዲሁም ወደ የወንጀል ሰለባዎች የእርዳታ መስመር በ1800 819 817 ላይ መደወል ይችላሉ። አስተርጓሚዎች አሉ።
- በመላ ሜልቦርን ባሉ የሕጻናት ማቆያ ማዕከላት በልጆች ላይ በተፈጸመው የጾታ ጥቃት በልጅዎ ላይ ተጽኖ ካገኙ፣ ነፃ የሆነ የምክር አገልግሎት በ 1800 791 241 አለ። አስተርጓሚዎች አሉ።
- የመኪና አደጋ አጋጥሞዎት ከሆነ አምበር ማህበረሰብን - የመንገድ ችግር ድጋፍ እና ትምህርት በ (03) 8877 6900 ወይም 1300 367 797 ያግኙ።
ከዚህ ምክር ማግኘት ይችላሉ፥
- የሕይወት መስመር ቴለ. 13 11 14
- የሀዘን መስመር ቴለ. 1300 845 745
- ከሰማያዊ በላይቴለ. 1300 22 4636
- ነርስ-በጥሪ ቴለ. 1300 60 60 24 – ለኤክስፐርት የጤና መረጃ እና ምክር (24 ሰዓታት፣ 7 ቀናት)
- የአውስትራሊያ የወላጅነት በይነመረብ - raisingchildren.net.au
እንዲሁም ይህን የስሜት ቀውስ እና የመልሶ ማገገም ፖድካስት ማዳመጥ ይችላሉ።
ለስሜት ቀውስ እና ለማገገም በቋንቋዎ መረጃ ለማግኘት የጤና ትርጉሞችን ይጎብኙ።
ለስሜት ቀውስ እንዴት ምላሽ መስጠት እንደሚችሉ
ለስሜት ቀውስ ምላሽ የሚሰጡበት መንገድ በሚከተሉት ላይ ሊመረኮዝ፥ ይችላል፥
- የስሜት ቀውሱ አይነት እና ክብደት
- ከዚህ በፊት ልምድ ወይም ስልጠና መኖር
- እርስዎ በቀጥታ የተሳተፉ ወይም ተመልካች ከሆኑ
- ከክስተቱ በኋላ ለእርስዎ የሚገኘው የእርዳታ መጠን
- በህይወትዎ ውስጥ የሚከናወኑ ሌሎች አስጨናቂ ነገሮች
- አስጨናቂ ክስተቶችን በመደበኛነት እንዴት እንደሚቋቋሙ
- ከዚህ ቀደም የነበሩ ማንኛውም አሰቃቂ ተሞክሮዎች።
አንድ አስጨናቂ ክስተት ሲያልቅ፣ ለክስተቱ ትርጉም ለመስጠት እየሞከሩ ሊሆን ይችላል። ይህ የሚከተሉት ማሰብን ሊያካትት ይችላል፥
- እንዴት እና ለምን እንደተከሰተ
- እንዴት እና ለምን ተሳትፈዋል
- የሚሰማዎት ስሜት ለምን እንደሚሰማዎት
- የሚሰማዎት ስሜት ምን አይነት ሰው እንደሆኑ ይጠቁማል ወይ
- ልምዱ በህይወት ላይ ያለዎትን አመለካከት ቀይሮ እንደሆነ እና እንዴት።
እንዲሁም ስሜታዊ፣ አእምሯዊ፣ አካላዊ እና ባህሪያዊ ምላሽ ሊሰማዎት ይችላል።
ስሜታዊ ምላሾች ለስሜት ቀውስ
እነዚህን ሊሰማዎት ይችላል፥
- በጣም የተጨነቀ፣ የተወጠረ ወይም ፈርቷል
- ሌላ ነገር እንደሚፈጠር ደንግጠዋል
- አደጋ ላይ እንዳሉ
- የደነዘዘ ወይም የተደናገጠ
- ግራ መጋባት
- ብዙ ጊዜ ስሜታዊ እና ብስጩ
- በጣም ድካም እና መሰልቸት
- የመንፈስ ጭንቀት
- ቤተሰብን ጨምሮ የሌሎችን ጥበቃ እና እና ጓደኞች
- ከቤትዎ መውጣት እንደማይፈልጉ
- ከሰዎች እና ቦታዎች መውጣት ወይም ማስወገድ እንደሚፈልጉ።
እነዚህ ምላሾች የተለመዱ ናቸው፣ እና አብዛኛዎቹ እነዚህ ምላሾች በአንድ ጊዜ ሊሰማዎት ይችላል።
የሰውነትዎ ተፈጥሯዊ የፈውስ እና የማገገም ሂደት አካል ነው፡ እና በአብዛኛዎቹ ሁኔታዎች ጥሩ ስሜት ይሰማዎታል።
የአእምሮ ምላሾች ለስሜት ቀውስ
እነዚህን ሊያጋጥምዎት ይችላሉ፥
- በትኩረትዎ ወይም ነገሮችን በማስታወስ ላይ ችግር ሊኖርብዎት
- በማይፈልጉበት ጊዜ ስለ ክስተቱ ማሰብ
- ክስተቱን በአእምሮዎ ውስጥ ደጋግመው ማጫወትዎን መቀጠል
- መደነገገር ወይም ግራ መጋባት።
አካላዊ ምላሽ ለስሜት ቀውስ
ሰውነትዎ የሚከተሉትን ሊያደርግ ይችላል፥
የባህሪ ምላሽ ለስሜት ቀውስ
እነዚህን ሊፈልጉ ይችላሉ፥
- ክስተቱን ከማስታወስ ሊቆጠቡ
- ስለተፈጠረው ነገር ማሰብ እና ማውራት መቀጠል
- ከእለት ወደ እለት የሚያደርጉዋቸው ነገሮች መቀየር ወይም ከማድረግ መቆጠብ
- በጣም የበዛ ወይም በጣም ያነሰ መብላት
- ተጨማሪ አልኮል እና/ወይም ቡና መጠጣት
- ማጨስ ሲጋራዎች
- እንቅልፍን ማስወገድ።
ከስሜት ቀውስ በኋላ እንዴት እንደሚድኑ እና እንደሚያገግሙ
ደህንነትዎን ወይም የሌሎችን ሕይወት አደጋ ላይ የሚጥል ማንኛውም ነገር ውጥረት እንዲሰማዎት ያደርጋል። ይህ 'የአደጋ ጊዜ ሁነታ' ይባላል እና ሰውነትዎ ለአደጋ ምላሽ ለመስጠት ሲሞክር ነው። ሰውነታችን ህልውናችንን ለመርዳት በአጭር ጊዜ ውስጥ ብዙ ጉልበት ሊሰጠን እየሞከረ ነው።
ብዙ ሰዎች 'በድንገተኛ ሁኔታ' ውስጥ ለአጭር ጊዜ ይቆያሉ። ነገር ግን ያልተጠበቁ ነገሮች ሲከሰቱ ወይም እንደገና በውጥረት ውስጥ ሲሆኑ ወደ 'ድንገተኛ ሁነታ' መመለስ ይችላሉ። ለዚህ ነው ከስሜት ቀውስ ክስተት በኋላ ድካም ሊሰማዎት የሚችለው።
ሰውነትዎ እንዲድን እና እንዲያገግም ለማገዝ፣ እራስዎን ከ'አደጋ ሁነታ' ለመውጣት መርዳት አለብዎት። ሰውነትዎ ወደ መደበኛው የኃይል መጠን እንዲመለስ እና እንዲጠገን ይረዳል። ይህ ብዙውን ጊዜ የሚሆነው በክስተቱ አንድ ወር ወይም ከዚያ ባለው ጊዜ ውስጥ ነው።
ለመዳን እና ለማገገም የሚረዱዎት ብዙ ስልቶች አሉ። እነዚህን ማድረግ ይችላሉ፥
- በሚያስጨንቅ ወይም በሚያስፈራ ልምድ ውስጥ እንዳለፉ ይወቁ። የእርስዎ ምላሽ የተለመደ ነው
- እንደ እራስዎ እንደማይሰማዎት ይቀበሉ፣ ግን ይህ ያልፋል
- እንደተለመደው ነገሮችን ማድረግ ካልቻሉ በራስዎት ላለመናደድ ወይም ላለመበሳጨት ይሞክሩ
- ለመቋቋም እንዲረዳዎ አልኮል ወይም ንዛዥ ዕፅ ከመጠቀም ይቆጠቡ
- ጥሩ ስሜት እስኪሰማዎት ድረስ ዋና ዋና ውሳኔዎችን ወይም ትልቅ የህይወት ለውጦችን ማድረግ ያስወግዱ
- ወደ መደበኛ ህይወትዎ ለመመለስ ጊዜዎን ይውሰዱ
- ሊያግዝዎ የሚችል እና ሊረዳዎ የሚችል ሰው ያነጋግሩ
- መደበኛ ስራዎን ለመጠበቅ ይሞክሩ እና በስራ ይጠመዱ
- አንዳንድ ቦታዎችን ወይም እንቅስቃሴዎችን ለማስወገድ ከመንገድዎ ላለመሄድ ይሞክሩ
- ለማረፍ ጊዜ መድቡ
- ለመደበኛ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ጊዜ ይስጡ
- ለቤተሰብዎ እና ለጓደኞችዎ ምን ዓይነት እርዳታ እንደሚፈልጉ ይንገሩ፣ ለምሳሌ ጊዜ ማሳለፊያ ወይም አንድ ሰው ለማነጋገር
- እንደ ዮጋ፣ መተንፈስ ወይም ማሰላሰል ያሉ የመዝናኛ ዘዴዎችን ይጠቀሙ። እንዲሁም የሚወዷቸውን ነገሮች ለምሳሌ ሙዚቃ ማዳመጥ ወይም አትክልት መንከባከብ ይችላሉ
- ስሜትዎን እንደተሰማዎት ይግለጹ። ስለ ስሜቶችዎ ከአንድ ሰው ጋር መነጋገር ወይም መጻፍ ይችላሉ
- ትውስታዎችዎን እና ልምዶችዎን እንደተሰማዎት ይጋፈጡ። አስቡባቸውና ወደ ጎን አስቀምጥዋቸው። ሌሎች ትውስታዎችን ካመጣ፡ አሁን ካለው ችግር ለመለየት ይሞክሩ።
አሁንም እየታገሉ ከሆነ የባለሙያ እርዳታ ማግኘት ይችላሉ
በስሜት ቀውስ የሚከሰት ውጥረት ቀጣይነት ያለው ሊሆን ይችላል። የሚከተሉትን ካጋጠምዎት የባለሙያ እርዳታ ማግኘት አለብዎት፥
- ከክስተቱ በኋላ ከአንድ ወር ወይም ከዚያ በላይ በሆነ ጊዜ ውስጥ በጣም ስሜታዊ ጭንቀት ካለቦት
- የመደንዘዝ እና የባዶነት ስሜትዎን ከቀጠለ
- የጭንቀት አካላዊ ምልክቶችን ማሳየትዎን ከቀጠለ
- የሚረብሽ እንቅልፍ ወይም ቅዠት ከቀጠለ
- የእርስዎን ልምዶች የሚያስታውስዎትን ማንኛውንም ነገር ለማስወገድ እየሞከሩ ከሆነ
- ስሜትዎን ለማጋራት ማንም ሰው ከሌሎት
- ከቤተሰብ እና ከጓደኞች ጋር ያለው ግንኙነት ጥሩ ኣለመሆኑን ካገኙ
- እየተዘናጉ ከሆነ
- ተጨማሪ አልኮል ወይም አደንዛዥ ዕፅ እየተጠቀሙ ከሆነ
- ወደ ሥራ መመለስ ወይም የዕለት ተዕለት ኃላፊነቶችን ማስተዳደር ካልቻሉ
- የስሜት ቀውስ ክስተት እንደገና ማጫወትዎን ከቀጠሉ
- ሁል ጊዜ ፍርሃት የሚሰማዎት እና በቀላሉ የሚደናገጡ ሊሆኑ ይችላሉ።
ስለ ድኅረ-የስሜት ቀውስ ህመም (PTSD)
ከአስጨናቂ ክስተት በኋላ፣ አንዳንድ ሰዎች ከአንድ ወር ወይም ከዚያ በላይ ያህል ከቆዩ በኋላ ጤናማ እንዳልሆኑ ይገነዘባሉ።
እንዲህ ዓይነቱ ምላሽ ሕይወትዎን በብዙ መንገዶች ሊጎዳ ይችላል። ከቤተሰብ እና ከጓደኞች ጋር ያለዎትን ግንኙነት ሊለውጥ ወይም ለመስራት ሊያከብድቦዎት ይችላል።
ይህ ድኅረ-የስሜት ቀውስ ህመም ወይም PTSD ሊሆን ይችላል።
PTSD እያጋጠመኝ ነው ብለው የምያስቡ ከሆነ፣ ከጤና ባለሙያ እርዳታ መጠየቅ አለብዎት።
በማንኛውም ጊዜ ስለ አእምሮዎ ጤንነት ወይም ስለሚወዱት ሰው የአእምሮ ጤንነት የሚጨነቁ ከሆነ በ 13 11 14 ላይፍላይን ይደውሉ።