ስለነጎድጓዳማ ዝናብ አስም ማስጠንቀቂያዎች፣ ምልክቶችና ህክምና ይወቁ። ለዚህ የሳር አበባ ብናኝ ወቅት ዝግጁ ይሁኑ።
የነጎድጓዳማ ዝናብ አስም ምንድን ነው?
በቪክቶሪያ፣ የሳር አበባ ብናኝ ወቅት አብዛኛውን ጊዜ ከኦክቶበር 1 እስከ ዲሴምበር 31 ይቆያል። በዚህ ጊዜ የአስምና የድርቆሽ ትኩሳት (ሄይ ፊቨር) መጨመር ሊያስተውሉ ይችላሉ። ወቅቱ የነጎድጓዳማ ዝናብ አስም የመከሰት እድልን ያመጣል።
የነጎድጓዳማ ዝናብ አስም በአየር ውስጥ ብዙ የሳር አበባ ብናኞች እና የተወሰነ አይነት የነጐድጓድ ዝናብ ሲኖር ሊከሰት ይችላል። የሳር አበባ ብናኝ ነፋስ ጠርጎ ረጅም ርቀት ድረስ ሊሸከመው ይችላል። አንዳንዶቹ ብናኞች ፈንድተው በጣም ጥቃቅን ቅንጣቶችን ሊለቁ ይችላሉ እነዚህም ነጎድጓዳማ ዝናብ ከመከሰቱ በፊት በሚመጣው የነፋስ ግፊት ይከማቻሉ። እነዚህ ጥቃቅን ቅንጣቶች ሰዎች በሚተነፍሱበት ጊዜ ጠልቀው ወደ ሳምባቸው በመግባት የአስም ምልክቶችን በፍጥነት ያስነሳሉ፣ ከዚህ በፊት አስም ኖሯቸው በማያውቁም ሰዎች ጭምር።
ብዙ ሰዎች በእነዚህ ሁኔታዎች ውስጥ በአጭር ጊዜ ውስጥ የአስም ምልክቶች ሲታዩባቸው፣ ይህ ወረርሽኝ የነጎድጓዳማ ዝናብ አስም በመባል ይታወቃል።
አደጋ ላይ ያለው ማን ነው?
ለነጎድጓዳማ ዝናብ አስም የሚጋለጡ ሰዎች ወቅታዊ ወይም ያለፈ አስም ያለባቸው፣ ያልታወቀ አስም ያለባቸው ወይም የፀደይ ወቅት የድርቆሽ ትኩሳት (ሄይ ፊቨር) ያለባቸውን ያጠቃልላል። አስም እና የኣፍንጫ ኣለርጂ ባለባቸው ሰዎች በተለይም አስም በደንብ የማይቆጣጠሩት ከሆነ አደጋው ከፍ ያለ ነው።
በዚህ የሳር አበባ ብናኝ ወቅት እራስዎን ይጠብቁ
የሚከተሉትን ቀላል እርምጃዎችን በመከተል በእርስዎ እንክብካቤ ሥር ያሉትን መጠበቅ ይችላሉ፦
- የነጎድጓዳማ ዝናብ አስም ወረርሽኝ ስጋት ትንበያ ይከታተሉ፦
- የቪክቶሪያ የድንገተኛ አደጋ/Vic Emergency የነጎድጓዳማ ዝናብ አስም ትንበያ ይጎብኙ
- የቪክቶሪያ የድንገተኛ አደጋ መተግበሪያን/VicEmergency በ AppStore ወይም Google Play ይጫኑ።
- ነጎድጓዳማ ዝናብ ሲኖር ከቤት ውጭ አይሁኑ፣ በተለይም ከነጎድጓድ ዝናብ በፊት ንፋስ በሚመጣበት ወቅት። ወደ ውስጥ ይግቡና በሮችዎን እና መስኮቶችዎን ይዝጉ። አየርን ከውጭ ወደ ቤት ወይም ወደ መኪና የሚያመጡትን የአየር ማጤዣዎች/ኮንዲሽነር ዘዴዎች ያጥፉ (በእንፋሎት የሚሰሩ የአየር ማጤዣዎችን ጨምሮ)።
- መመሪያውን ተከትለው የመከላከያ መድሃኒትዎን ይውሰዱ።
- የአስም በሽታን እንዴት እንደሚቆጣጠሩ ይወቁ። የአስምዎን የድርጊት መርሃ ግብር ይከተሉ ወይም የአስም የመጀመሪያ እርዳታን ይጠቀሙ።
አስም
- አስም ካለብዎ - የአስም መቆጣጠሪያዎን ለመፈተሽ ሀኪምዎን ያነጋግሩ እና የአስምዎን የድርጊት መርሃ ግብር ይከልሱ እና ያዘምኑ ትክክለኛው የአስም መድሃኒት እንዳለዎት እና በትክክል እየተጠቀሙበት መሆኑንም ያረጋግጡ። ያስታውሱ፣ እንደ መመሪያው የአስም መከላከያ መውሰድ ወሳኝ ነው። የነጎድጓዳማ ዝናብ አስምን ጨምሮ የአስም ምልክቶችን ለመከላከል ይረዳል።
- አስም አጋጥሞዎት የሚያውቁ ከሆነ - ራስዎን ከነጎድጓዳማ ዝናብ አስም አደጋ ስለመጠበቅ ሐኪምዎን ያነጋግሩ።
- ሲተነፍሱ ድምጽ፣ የትንፋሽ ማጠር፣ የደረት መጨናነቅ፣ ወይም የማያቋርጥ ሳል ካለብዎት - ሐኪምዎን ያነጋግሩ። አስም እንዳለብዎት እና እነዚህን ምልክቶች እንዴት መቆጣጠር እንደሚችሉ ለማወቅ ይረዱዎታል።
- ሁልጊዜ የማስታገሻ መድሃኒትዎን ይያዙ - ይህ የእርስዎ የድንገተኛ የአስም የመጀመሪያ እርዳታ መድሃኒት ነው።
ለአነስተኛ የአስም ምልክቶች፣ ጠቅላላ ሐኪምዎን ይጎብኙ፣ ከፋርማሲስት ጋር ይነጋገሩ ወይም ሌሎች የእንክብካቤ አማራጮችን ይጠቀሙ። ሁኔታዎ ካልተሻሻለ ወይም እየተባባሰ ከሆነ ወደ 000 ይደውሉ ወይም ወደ ሆስፒታል ይሂዱ።
የድርቆሽ ትኩሳት (ሄይ ፊቨር)
- የፀደይ ወቅት የድርቆሽ ትኩሳት (ሄይ ፊቨር) ካለብዎት፣ ፋርማሲስትዎን ወይም ሐኪምዎን/GP ያነጋግሩ። የድርቆሽ ትኩሳት (ሄይ ፊቨር) ህክምና እቅድ እንዲያዘጋጁ እና እራስዎን ከነጎድጓዳማ ዝናብ የአስም በሽታ የሚከላከሉበትን መንገዶች ሊጠቁሙዎት ይችላሉ። ይህ የነጎድጓዳማ ዝናብ አስም ቢያጋጥምዎት የአስም ማስታገሻ በፍጥነት የት እንደሚያገኙ ማወቅን ይጨምራል - እነዚህ ያለ ሐኪም ማዘዣ ከፋርማሲዎች ይገኛሉ።
- የአስም ምልክቶች ከታየብዎት፣ የአስም በሽታ የመጀመሪያ እርዳታ ደረጃዎችን ይከተሉ እና ሐኪምዎ/GP ጋር ክትትል ማድረግዎን ያረጋግጡ።
- ማናቸውም የአስም ምልክቶች የድርቆሽ ትኩሳት (ሄይ ፊቨር) ጋር ካጋጠምዎት ወይም እርግጠኛ ካልሆኑ፣ ሐኪምዎን ይጎብኙ። ምርመራ ከተደረገ በኋላ ጥሩ ስሜት እንዲሰማዎት እና እንዲተነፍሱ የሚያደርግ ውጤታማ ህክምና ሊያገኙ ይችላሉ።
የአስም በሽታ የመጀመሪያ እርዳታ
የአስም በሽታ የመጀመሪያ እርዳታን ማወቅ በማህበረሰቡ ውስጥ ላለ ለሁሉም ሰው አስፈላጊ ነው። የአስም የመጀመሪያ እርዳታ መረጃ ከከበተር ሄልዝ ቻነል፣ ከአስም እና ከብሔራዊ የአስም ካውንስል ይገኛል።
የሚከተሉት ከሆኑ ወዲያውኑ ወደ ሦስት ዜሮ (000) ይደውሉ፡-
- ሰውዬው የማይተነፍስ ከሆነ
- አስሙ በድንገት እየባሰ ከሄደ ወይም እየተሻሻለ ካልሆነ
- ሰውዬው የአስም በሽታ ጥቃት እያጋጠመው ከሆነ እና ምንም ማስታገሻ መድሃኒት ከሌለ
- ሰውዬው አስም ስለመሆኑ እርግጠኛ ካልሆነ
- ሰውዬው አናፊላክሲስ/ለህይወት ኣስጊ የሆነ የኣለርጂ ችግር እንዳለበት የሚታወቅ ከሆነ። ጉዳዩ ይህ ከሆነ፣ ሁልጊዜ በመጀመሪያ አድሬናሊን አውቶኢንጀክተር የሚባለውን ይስጡት፣ ከዚያም የቆዳ ምልክቶች ባይኖሩም ሪሊቨር/ማስታገሻ ይስጡት።
ይህንን መረጃ በሌሎች ቋንቋዎች ለማግኘት ወደ የተርጓሚና እና አስተርጓሚ አገልግሎት (TIS በ 131 450 (የነጻ ጥሪ) የደውሉ እና ወደ ተረኛ ነርስ እንዲደውሉ ይጠይቋቸው።
መስማት የተሳንዎት ከሆኑ፣ የመስማት ችግር ካለብዎት፣ ወይም የንግግር/የግንኙነት እክል ካለብዎት ብሔራዊ ቅብብሎሽ አገልግሎት/National Relay Service ን ያነጋግሩ እና ወደ ተረኛ ነርስ እንዲደውሉ ይጠይቋቸው።
ተዛማጅ መረጃ
- በተር ሄልዝ ቻነል የነጎድጓዳማ ዝናብ አስም ድረ-ገጽ
- የነጎድጓዳማ ዝናብ አስም
- የሜልበርን የአበባ ብናኝ ወይም መተግበሪያ
- አስም አውስትራሊያ/Asthma
- ብሔራዊ የአስም ካውንስል አውስትራሊያ/National Asthma Council
እርዳታ የት እንደሚገኝ
- በድንገተኛ አደጋ ሁል ጊዜ ወደ ሦስት ዜሮ ይደውሉ (000)
- በቪክቶሪያ ውስጥ አስቸኳይ እንክብካቤ አገልግሎቶች
Content disclaimer
Content on this website is provided for information purposes only. Information about a therapy, service, product or treatment does not in any way endorse or support such therapy, service, product or treatment and is not intended to replace advice from your doctor or other registered health professional. The information and materials contained on this website are not intended to constitute a comprehensive guide concerning all aspects of the therapy, product or treatment described on the website. All users are urged to always seek advice from a registered health care professional for diagnosis and answers to their medical questions and to ascertain whether the particular therapy, service, product or treatment described on the website is suitable in their circumstances. The State of Victoria and the Department of Health shall not bear any liability for reliance by any user on the materials contained on this website.