ማጠቃለያ
Read the full fact sheet- ልጅዎን ከአስጨናቂ ወይም ከአስፈሪ ገጠመኞች እንዲያገግም መርዳት ይችላሉ። እነዚህ ልምዶች የሚከተሉትን ሊያካትቱ ይችላሉ፥ የመኪና አደጋዎች የጫካ እሳቶች ወይም ጎርፎች በቤተሰብ ውስጥ ድንገተኛ ህመም ወይም ሞት ወንጀል፡ ጉዳት (ስድብ) ወይም ጥቃት
- ልጆች የሚከተሉትን ይፈልጋሉ፥ ቀውሱን እርስዎ እንዴት እንደሚቋቋሙት እርስዎ ለልጆቹ ስሜት እና ባህሪ እንዴት ምላሽ እንደሚሰጡ
- እነዚህ ምክሮች ከልጅዎ ጋር ስለ ተሞክሯቸው እንዲወያዩ ሊረዱዎት ይችላሉ። ለልጅዎ በእድሜው ሊረዳው በሚችልበት መንገድ እውነታውን መንገር አስፈላጊ ነው።
- ሁልጊዜ የባለሙያ እርዳታ መጠየቅ ይችላሉ። ለመጀመር ጥሩ ቦታ የቤተሰብዎ ኣጠቃላይ ሓኪም ነው።
On this page
ልጆች ለስሜት ቀውስ እንዴት ምላሽ ይሰጣሉ
አንድ ልጅ ለአስጨናቂ ወይም ለአስፈሪ ገጠመኝ የሚሰጠው ምላሽ በሚከተሉት ላይ የተመሮኮዘ ሊሆን ይችላል፥
- እድሜያቸው
- የእነሱ ስብዕና
- እርስዎ ወይም ቤተሰብዎ እንዴት ምላሽ እየሰጡ እንደሆነ
ልጅዎ እርስዎ በሚጠብቁት መንገድ ምላሽ ላይሰጥ ይችላል። ምናልባት የሚከተሉትን ሊያረጉ ይችላሉ፥
- የተገለሉ - ለእንቅስቃሴዎች ፍላጎታቸውን ሊያጡ ይችላሉ። እንዲሁም ትንሽ በራስ የመተማመን ስሜት ሊኖራቸው፣ ጸጥ ሊሉ ወይም ልጅ በነበሩበት ጊዜ ያሳዩት ወደነበረ ባሕሪያቸው ሊመለሱ ይችላሉ።
- በሃሳብ የተዋጡ - ልምዱን እንደገና ማደስ ያስፈልጋቸው ይሆናል። ለምሳሌ፡ በድግግሞሽ ጨዋታ ወይም ስዕሎች። ልጅዎ ስለወደፊቱ ክስተቶች ሊፈራ ወይም ቅዠት ሊኖረው ይችላል።
- ጭንቀት (ውጥረት) - ትኩረትን የመሰብሰብ ወይም የመስጠት ችግር ሊኖርባቸው ይችላል። ሁል ጊዜ ከእርስዎ ጋር መሆን የሚፈልጉ፣ የእንቅልፍ ችግር ያለባቸው ወይም በቀላሉ የሚበሳጩ ሊሆኑ ይችላሉ።
- ደህና አለሞሆን - ራስ ምታት እና የሆድ ህመም ሊኖራቸው ይችላል።
ልጅዎ የዘገየ ምላሽ ሊኖረው ይችላል። አንዳንድ ልጆች ጥሩ ሊመስሉ ይችላሉ፣ ግን ከቀናት፣ ከሳምንታት ወይም ከወራት በኋላ ምላሽ ሊሰጡ ይችላሉ።
ስለ የስሜት ቀውስ ክስተት እንዴት ማውራት እንደሚቻል
ለልጅዎ ታማኝ ከሆኑ ልጅዎን ይረዳል።የሚከተሉትን ማድረግ ይችላሉ። የሚከተሉትን ማድረግ ይችላሉ፥
- ልጅዎ ደህንነቱ የተጠበቀ መሆኑን እና ክስተቱ እንዳለቀ ያረጋግጡለት። ብዙ ጊዜ ማረጋጋት ሊኖርብዎ ይችላል።
- ልጅዎን ያዳምጡ። ጭንቀታቸውን እና ስሜታቸውን በቁም ነገር ይያዙ።
- ልጅዎ ምን እንደሚሰማው መስማት እንደሚፈልጉ ያሳውቁ።
- ከዕድሜው ጋር በሚስማማ መንገድ ስለተፈጠረው ነገር ለልጅዎ ይንገሩ። ሊረዱትን የሚችሉ ቋንቋ ይጠቀሙ። ልጅዎ መሠረታዊ የሆኑትን እውነታዎች የማያውቅ ከሆነ፣ የተፈጠረውን ነገር በራሳቸው ለመፍታት ሊሞክሩ ይችላሉ። ታሪኩን ለማጠናቀቅ ሃሳባቸውን ወይም ውስን መረጃን ሊጠቀሙ ይችላሉ። ይህ ለልጅዎ የበለጠ ጭንቀት እና ግራ መጋባት ሊፈጥር ይችላል።
- ልጅዎ ጥፋታቸው እንዳልሆነ እንደሚያውቅ እርግጠኛ ይሁኑ። ባለጌ ከሆኑ ወይም ስለ አንድ ሰው መጥፎ ነገር ካሰቡ ይህን ያስቡ ይሆናል።
- ስለ ክስተቱ እንደ ቤተሰብ ማውራት። ልጆችን ጨምሮ ሁሉም ሰው የራሱን አስተያየት እንዲሰጥ ይፍቀዱ። ይህ ሁሉም ሰው እንደሚደገፍ፣ እንደሚሰማ እና እንደሚረዳ እንዲሰማው ይረዳል።
- ሰዎች ለጭንቀት እንዴት ምላሽ ሊሰጡ እንደሚችሉ ከልጅዎ ጋር ይነጋገሩ። በእነዚህ ሁኔታዎች ስሜታቸው የተለመደ መሆኑን እና ኣዲስ ነገር ኣለመሆኑን ይንገሯቸው። በጊዜ ሂደት ጥሩ ስሜት እንደሚሰማቸው ሊያረጋግጡላቸው ይችላሉ።
ስለ የስሜት ቀውስ ክስተት እንዴት ምላሽ መስጠት እንደሚቻል
ለልጅዎ ስሜት እና ባህሪ የእርስዎ ምላሽ በማገገም ላይ ተጽዕኖ ይኖረዋል። የሚከተሉትን ቱክረት መስጠት አስፈላጊ ነው፥
- በባህሪያቸው ላይ ስላለው ለውጥ መረዳት። ልጆች ለአስጨናቂ ወይም ለአስፈሪ ክስተቶች በተለያየ መንገድ ምላሽ ይሰጣሉ። እንደ መበሳጨት ወይም አልጋ ማራስ (ለሊት ኣልጋ ላይ መሽናት) ያሉ የባህሪያቸው ለውጦች የተለመደ ነው።
- ለልጅዎ ተጨማሪ ትኩረት ይስጡ። ይህ በመኝታ ሰዓት እና በሌሎች የመለያየት ጊዝያቶች አስፈላጊ ሊሆን ይችላል።
- ለራስዎ እርዳታ ያግኙ። ልጆች ችግርን ለመረዳት እና ምላሽ ለመስጠት ወላጆቻቸውን ወይም ተንከባካቢዎቻቸውን ይመለከታሉ። ፍርሃታቸውን እንዲረዱ እና እንዲያጽናኗቸው በዙሪያቸው ያሉ አዋቂዎች ያስፈልጋቸዋል። ከተጨነቁ፣ እርስዎም ድጋፍ ማግኘት ይችላሉ። ካላደረጉት ልጅዎ የሚሰማውን ፍርሃት እና ጭንቀት ይጨምራል።
- ከልጅዎ ጋር በተገቢው መንገድ ስለ ስሜቶችዎ ይናገሩ። ይህም ስለ ራሳቸው እንዲናገሩ ሊረዳቸው ይችላል።
- ሁሉም ሰው የተለየ እንደሆነ እና የተለየ ስሜት ሊኖረው እንደሚችል ያስታውሱ። ልጅዎ እርስዎ እንደሚሰማዎት አይነት ስሜት እንዲሰማው አይጠብቁ።
- ልጅዎ በሕይወቱ ላይ የመቆጣጠር ስሜት እንዲሰማው ያድርጉ። ጥቃቅን ውሳኔዎችን ማድረግ እንኳን የበለጠ የመቆጣጠር ስሜት እንዲሰማቸው ሊያደርግ ይችላል። ይህ በተለይ ከችግር ቀውስ በኋላ በጣም አስፈላጊ ነው። አቅመ ቢስነት የሚሰማቸው ልጆች የበለጠ ጭንቀት ሊሰማቸው ይችላል።
- ልጅዎን ከመጠን በላይ ላለመጠበቅ ይሞክሩ። ከችግር በኋላ ቤተሰብዎን በማቀራረብ ማቆየት መፈለግዎ የተለመደ ነው። ነገር ግን የእነሱ ዓለም አስተማማኝ ቦታ እንደሆነ እንዲሰማቸው መርዳት አስፈላጊ ነው።
ከስሜት ቀውስ ክስተት በኋላ የቤተሰብ ልምዳዊ ድርጊቶች
የሚከተሉትን ቱክረት መስጠት አስፈላጊ ነው፥
- በተቻለ መጠን መደበኛ ልምዳዊ ድርጊትዎን ይቀጥሉ። ይህ ለልጆች የሚያረጋጋ ነው።
- ልጅዎን የተለመደውን ተግባሩን ማስተዳደር ካልቻለ ያረጋጉት። ይህ ትምህርት ቤት መከታተል ወይም የቤት ውስጥ ሥራዎችን መሥራት ይጨምራል።
- እንደ አዲስ የዕለት ተዕለት ተግባራት፣ ኃላፊነቶች ወይም በባህሪያቸው የሚጠበቁ ለውጦችን ከማስተዋወቅ ይቆጠቡ።
- በቤት ውስጥ እንደ ትልቅ ሰው ሚናዎን ይጠብቁ። እየታገሉ ከሆነ ለእርዳታ በልጅዎ ላይ አለመመርኮዝን አስፈላጊ ነው።
ልጅዎ እንዲያገግም እንዴት መርዳት እንደሚችሉ፥
የሚከተሉትን ቱክረት መስጠት አስፈላጊ ነው፥
- ልጅዎ እንዲጫወት ብዙ ጊዜ ይፍቀዱለት። ይህ ስፖርት፣ የሚወዷቸው ጨዋታዎች እና ከታወቁ ጓደኞች ጋር ያሉ እንቅስቃሴዎች ሊሆን ይችላል።
- ለመዝናናት ጊዜ ፍቀዱ። ሳቅ፣ ጥሩ ጊዜ እና የጋራ ደስታ ሁሉም የቤተሰብ አባላት ጥሩ ስሜት እንዲሰማቸው ሊረዳቸው ይችላል።
- የልጅዎ የምግብ ፍላጎት ሊለወጥ እንደሚችል ያስታውሱ። በምግብ ሰዓት መብላት የማይፈልጉ ከሆነ በምትኩ ቀኑን ሙሉ በሚመቻቸው ሰአት መደበኛ መክሰስ ያቅርቡላቸው።
- ልጅዎ በቂ እረፍት እና እንቅልፍ ማግኘቱን ያረጋግጡ።
- በአካል ብቃት እንቅስቃሴ እርዳቸው። ይህ በጭንቀት ላይ ያለ ልጅዎን ለመርዳት እና እንቅልፍን ለማሻሻል ይረዳል።
- ስኳር፡ ባለቀለም ምግቦች እና ቸኮሌት ይገድቡ።
- ልጅዎ በአካል እንዲዝናና እርዱት። ይህ በሞቀ ውሃ ገላ መታጠብ፣ ማሳጅዎች፣ የታሪክ ጊዜዎች እና ብዙ መተቃቀፍ ሊሆን ይችላል።
- ልጅዎን የሚያበሳጭ ወይም የሚያስጨንቅ ከሆነ እንቅስቃሴውን ይለውጡ። ለምሳሌ፣ ልጅዎን እንዲጨነቅ ወይም እንዲፈራ የሚያደርግ የቴሌቪዥን ትርኢት።
በማንኛውም ጊዜ ስለ አእምሮዎ ጤንነት ወይም ስለሚወዱት ሰው የአእምሮ ጤንነት የሚጨነቁ ከሆነ በ 13 11 14 ላይፍላይን ይደውሉ።
እርዳታ የት እንደሚገኝ
- የእርስዎ ኣጠቃላይ ሓኪም (ዶክተር)
- የእናቶች እና የልጅ ጤና ነርስ
- የአካባቢዎ የማህበረሰብ ጤና ጣቢያ
- የሕፃናት ሐኪም ወይም የሕፃናት እና ጎረምሶች የሥነ አእምሮ ሐኪም - ሐኪምዎ ሊልክዎ ይችላል
- ፎኒክስ አውስትራሊያ የድህረ-የስሜት ቀውስ አእምሯዊ ጤና ማዕከልቴለ. (03) 9035 5599
- የሀዘን እና የዘመድ ሞት ሀዘን ማዕከል ቴለ. 1800 642 066
እንዲሁም ከዚህ ምክር ማግኘት ይችላሉ፥
- የሕይወት መስመር ቴለ. 13 11 14
- የሀዘን መስመር ቴለ. 1300 845 745
- ከሰማያዊ በላይቴለ. 1300 22 4636
- የልጆች እገዛ መስመር ቴለ. 1800 55 1800
- ነርስ-በጥሪ ቴለ. 1300 60 60 24 – ለኤክስፐርት የጤና መረጃ እና ምክር (24 ሰዓታት፣ 7 ቀናት)
- የአውስትራሊያ የወላጅነት በይነመረብ - raisingchildren.net.au